አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ 22ኛውን የስነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ቀን “ትውልድን በስነ ምግባር ተቋምን በአሰራር” በሚል መሪ ቃል አከበረ፤
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ፤ ህዳር 15፣ 2018
አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ 22ኛውን የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ቀን “ትውልድን በስነ ምግባር ተቋምን በአሰራር” በሚል መሪ ቃል አክብሯል፣ በክብረ በዓሉ ላይም የከተማችን የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ስራዎች የተካተቱበት ሰነድ የቀረበ ሲሆን፡፡ ኮሌጁም በሁሉም የስራ ክፍሎቹና በትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ታማኝነትን፣ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን ለማስፈን ያለውን ቁርጠኝነቱን አረጋግጧል።
የበዓሉ አከባበር በኢትዮጵያ ብሎም በከተማ አስተዳደራችን አጠቃላይ የስነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ቀን አከባበር ጋር ተያይዞ ከሁለት አስርት አመታት በላይ ሲካሄድ የቆየው የሀቀኝነት እና የሃላፊነት እሴቶች በተቋማት ውስጥ እንዲሰፍን የማድረግ ጥረት ስራ ነው።
በበዓሉ አከባበርም የኮሌጁ ሰልጣኞች የጥያቄና መልስ ውድድር ያደረጉ ሲሆን ለአሸናፊዎች የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡
የኮሌጁ ዋና ዲን ወ/ሮ ጌጤነሽ ዘርአብዛ እንዳብራሩት የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ስራዎች ያለው የነቃ ተሳትፎ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ከሙስና የፀዳ የወደፊት ሁኔታን በመቅረጽ ረገድ መልካም የሚባል ተግባራትን ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡
በክብረበዓሉ ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞች እና አጋሮቻችን የታማኝነት እና የፍትሃዊነት እሴቶችን እንዲያስከብሩ፣ ተቋማችን በስነ ምግባር የታነፀ አመራርና የዘላቂ ልማት አንቀሳቃሽ ሆኖ እንዲቀጥል እንደሚሰራ ተገልቷል፡፡
<<ከፍታን ማፅናት፤ ነገን ማላቅ>>



.