Announcement የመስቀል እና ኢሬቻ በዓል አከባበር

የመስቀል እና ኢሬቻ በዓል አከባበር

25th September, 2025

የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የመስቀል እና ኢሬቻ በዓላትን "በእመርታና ማንሰራራት የታጀበ ህዝባዊ በዓላትን በጋራ እናክብር" በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ አከበረ

አዲስ አበባበ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተከብሯል ። በዓሉን አስመልክቶ የኮሌጁ ዋናዲን ወ/ሮ ጌጤነሽ ዘርአብዛን ጨምሮ የኮሌጁ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት፣ የሁለቱ ብሔራዊ በዓላት ትርጉምና የባህል እሴት ጎላ ብሎ ቀርቧል።

በመርሀግብሩ ላይ የኮሌጁ አሰልጣኝ የሆኑት ኢንስትራክተር ከቡ አየለ፣ የበዓላቱን ታሪካዊ አመጣጥ፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትርጉም የሚያብራራ ሰነድ አቅርበዋል ፣ሰነዱን ተከትሎም ከተሳታፊዎች ጋር በበዓላቱ ጠቀሜታ፣ በሀገር አንድነትና በመቻቻል ላይ ውጤታማ ውይይት ተደርጓል። ኢንስትራክተር ከቡ አየለ፣ የመስቀል በዓል የእምነት እና የብርሃን ምሳሌ መሆኑን፣ ኢሬቻ ደግሞ የምስጋና፣ የሰላምና የተፈጥሮ ፍቅር መገለጫ መሆኑን አስረድተዋል።
በበዓሉ መሰረትም፣ የኮሌጁ ሽማግሌዎች የዕለቱን ትርጉም ባገናዘበ መልኩ ለኮሌጁ ማህበረሰብ እና ለሀገር ሰላም፣ አንድነትና ብልጽግና ምርቃት መርቀዋል።

በተለይም የኮሌጁ ዋናዲን ወ/ሮ ጌጤነሽ ዘርአብዛ በዓላቱ የኢትዮጵያን የብዝሃነት ውበት እና ህዝቦች በአንድነትና በመከባበር የመኖር ባህል ማሳያ እንደሆኑ አጽንኦት ሰጥተዋል። 
የኮሌጁ አመራሮች እና ሰራተኞችም በዓሉን በማክበር የተሰማቸውን ደስታና ኩራት በመግለጽ፣ እንደዚህ አይነት ዝግጅቶች በኮሌጁ ማህበረሰብ ዘንድ ያለውን መተሳሰብና ትብብር እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል።

<< ከፍታን ማፅናት ነገን ማላቅ >>

አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን

.

Copyright © All rights reserved.

Created with