የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጁን ለአገልግሎት ምቹ ከማድረግ አንፃር ተጠግነው አገልግሎት መስጠት የማይችሉ እና መልሰው አገልግሎት ላይ የማይውሉ ንብረቶች እንዲወገዱ አደረገ፤
አዲስ አበባ፣ ህዳር 03/2018ዓ/ም፤ አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጁ ኮሌጁን ለአገልግሎት ምቹ ከማድረግ አንፃር ተጠግነው አገልግሎት መስጠት የማይችሉ ንብረቶችና ቁርጥራጭ ብረቶችን በከተማ አስተዳደሩ የንብረት ማስዎገድ ስነስርዓት መሰረት እንዲዎገዱ አድርጓል፡፡ በዚህ ስራም ኮሌጁ 1220 ኪሎግራም ብረታብረት፣580 ኪሎ ቁርጥራጭ የኤልክትሮኒክስ እቃዎች እንዲዎገዱ ያደረገ ሲሆን በተወገዱ ንብረቶችም 192,029 ብር ገቢ እንዲሆን መደረጉም የታወቀ ሲሆን በተጨማሪም ቁርጥራጭ እንጨቶች ለብሄራዊ ኢትዮጲያ 1 ኛ ደራጃ ት/ት በት በስጦታ ተበርክቷል ፡፡
ከዚህ ቀደም በተከታታይ ዓመታት በኮሌጁ ከፍተኛ መወገድ የሚገባቸው ንብረቶች ክምችት የነበረ ሲሆን በ2017 በጀት ዓመት ተወግደው ያልተጠናቀቁና የመስሪያ ቦታን ምቹ ለማድረግ እንቅፋት የነበሩ አላስፈላጊ ክምችቶች እንዲወገዱ እድል የፈጠረ ተግባር መሆኑ ተመላክቷል፡፡

.