Announcement በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ቅንጅታዊ ስራዎች አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የዕቅድ ውይይትና  የመግባቢያ ስምምነት መፈራረም ተካሄደ፤

በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ቅንጅታዊ ስራዎች አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የዕቅድ ውይይትና  የመግባቢያ ስምምነት መፈራረም ተካሄደ፤

29th August, 2025

በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ቅንጅታዊ ስራዎች አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የዕቅድ ውይይትና  የመግባቢያ ስምምነት መፈራረም ተካሄደ፤

አዲስ አበባ

በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ፣ ሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም. የኮሌጁን ቅንጅታዊ ስራዎች አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የዕቅድ ውይይትና  የመግባቢያ ስምምነት መፈራረም ተካሂዷል። በፕሮግራሙ ላይም የኮሌጁ ዋና ዲን ወ/ሮ ጌጤነሽ ዘርአብዛ የ2018ዓ/ም በጀት ዓመት ዕቅድ ያቀረቡ ሲሆን ተሳታፊ ባለድርሻ አካላት እቅዱን በጋራ ከማሳካት አኳያ ያላቸውን ገንቢ አስተያት ሰጥተዋል፤

ይህ ውይይት ኮሌጁ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር እና የጋራ ልማት ግቦችን ለማሳካት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሲሆን በመጨረሻም ከባለድርሻ አካላት በተነሱ ጉዳዮች ላይ የኮሌጁ ዋና ዲን አስተያየታቸውን ከሰጡ በኋላ የአራዳ ክፍለ ከተማ የተለያዩ ጽ/ቤቶች (የሥራና ክህሎት ፅ/ቤት፣ የኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት፣ የትምህርት ጽ/ቤት፣ የአረንጓዴ ውበትና ምናፈሻ ጽ/ቤት፣ ለወጣቶች ስፖርት ጽ/ቤት፣ የሴቶች፣ ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት፣ የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት) እንዲሁም የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የአራዳ/ቂርቆስ እና የካ ቅርንጫፎች ጋር የቅንጅታዊ ስራዎችን መሰረት በማድረግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን

.

Copyright © All rights reserved.

Created with