የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ለኮሌጁ ሴት ሰራተኞችና አመራሮች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጠ
ጥር 13/2018ዓ/ም፤ አዲስ አበባ፡- የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ለኮሌጁ ሴት ሰራተኞችና አመራሮች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል፤ ስልጠናው የኮሌጁ ሴት ሰራተኞችና አመራሮች በሊደርሽፕና ሰልፍ አዌርነስ አርዕስቶች ላይ የተሰጠ ሲሆን በስልጠና መርሀ ግብሩ ሴቶች ራሳቸውን፣ ተቋማቸውንና ብሎም ሀገራቸውን የሚያገለግሉበት መንገድ በእውቀትና ክህሎት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን የሚያስችል ሲሆን፤ ኮሌጁ በቀጣይ በተቋሙ የሚሰሩ ሴት ሰራተኞች አቅማቸውን የሚያጎለብቱበት የአቅም ግንባታ ስራዎችን በመስራት በከተማ አስተዳደራችን የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ እንደሚዎጣ ተብራርቷል፡፡
በስልጠና መርሀ ግብሩ አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የሥርዓተ-ፆታ ፍትሃዊነትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እና ሴቶችን በዘርፉ ለማብቃት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሲሆን በዚህም ሁሉን አሳታፊ አመራርን ለመገንባት አስቻይ ሁኔታዎችን የሚፈጥር ነው፡፡



.