አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ሰልጣኞችን አስመረቀ!
አዲስ አበባ
አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በተለያዩ ዲፓርትመንቶች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመረቀ። በምረቃው ስነስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤን ጨምሮ በርካታ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች እና የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ተመራቂዎቹ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ያለውን የሰው ኃይል ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችላቸውን እውቀትና ክህሎት ከኮሌጁ ማግኘታቸው ተገልጿል።
ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በዕለቱ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት፣ ተመራቂዎች ለሀገር ልማትና ዕድገት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን!