Announcement Arada ISO

Arada ISO

31st July, 2025

አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ISO 21001፡2018 EOMS ትግበራ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ – ሐምሌ 04፣ 2017ዓ/ም — የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት የአመራር ስርዓት ለማሻሻልና ደረጃቸውን የሚያስጠብቀውን የISO 21001፡2018 አለም አቀፍ ደረጃን ለመተግበር ጉዞውን በይፋ ጀምሯል። በዚህም የኮሌጁ አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት የማኔጅመንት ብሪፊንግ በማድረግ የትግበራ ሂደቱ ተጀምሯል፡፡
የትግበራው ዓላማም የኮሌጁን የትምህርትና ስልጠና አመራር ስርዓት ደረጃውን የተበቀ በማድረግ የስልጠና ጥራትን ማሻሻል፣ የሰልጣኝ ፍላጎቶች ማሟላትና ከዓለም አቀፍ የስልጠና ደረጃዎች ጋር በመጣጣም ቀጣይነት ያለው መሻሻል ማረጋገጥ ነው፡፡
በፕሮግራሙ ላይም ከኢትጵያ ደረጃዎች ኢንስቲቱት የተመደቡ ባለሙያዎች ኮሌጁ ያለበትን ነባራዊ መነሻ ካጠኑ በኋላ አስፈላጊ የማኔጅመንት ብሪፊንግ ስራዎችን ሰርተዋል፤ የኮሌጁ ዲን ወ/ሮ ጌጤነሽ ዘር አብዛ በበኩላቸው የ ISO 21001፡ 2018 ትግበራ እንደ አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ባሉ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ላይ የሰልጣኝ እርካታን እና የተሻሻሉ የአስተዳደር ስርዓቶችን በመጠቀም የስልጠና ውጤታማነትን በማሳደግ ኮሌጁ ተዓማኒነትን፣ ቅልጥፍናን እና ፈጠራዎችን ወደ አለማቀፋዊ ምርጥ ተሞክሮዎች የላቀ ደረጃን እንዲያሳድግ ያደርጋል፡፡
የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠናን ጥራት ለማሻሻል የ ISO 21001፡2018 ትግበራ መጀመር የተቋማዊ የስልጠና ጥራትና እና አመራር ስርዓትን በማሻሻል ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ነው፡፡
አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን

.

Copyright © All rights reserved.

Created with