Announcement Arada Manufacturing College Meeting

Arada Manufacturing College Meeting

28th July, 2025

አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2017 በጀት አመት አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም ውይይትና ግምገማ አደረገ።
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ – ሐምሌ 03፣ 2017ዓ/ም — በዚህ የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2017 በጀት አመት አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም ውይይትና ግምገማ የተለያዩ ክፍሎች ተሳትፈዋል በዚህም አካዳሚክ ዳይሬክቶሬቶች፣ አስተዳደራዊ ዳይሬክቶሬቶች፣ ቡድኖችና ጽ/ቤቶችን ያካተተ ሲሆን፣
ኮሌጁ በ2017 በጀት ዓመት እንዲከናወኑ ካቀዳቸው ግቦች፣ ዓለማዎችና ተግባራቶች አኳያ አፈጻጸሞች ያላቸውን ውጤታማነትና የተለያዩ ተግዳሮቶችን በመገምገም በቀጣይ በጀት ዓመት የተሻሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ውይይት ተደርጓል፡፡ እንደ ስልጠና ጥራት፣ የሰልጣኝና ተገልጋይ እርካታ፣ የኢንዳስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት፣ የቴክኖሎጅ ፋብሪኬሽንና የተቋማት ልማት ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ የተገመገሙ ሲሆን በተጨማሪም የኮሌጁ አስተዳደራዊ ስራዎች የስራ አፈጻጸም በመገምገም ለቀጣይ በጀት ዓመት ችግሮችን የመፍታት ባህልን በማጎልበትና ተገልጋይን ቅድሚያ በመስተት ብልሹ አሰራሮችን ያስወገደ አገልግሎት እንዲሰጥ በማስቻል ስራዎች እንዲፈጸሙ አቋም በመያዝ ተጠናቋል።
ይህ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተቋማዊ ውጤታማነትን ለማጠናከር ትርጉም ያለው ሲሆን ኮሌጁ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ የጥራት መሻሻል ላይ ያለውን አፈጻጸም እንዲያሻሽል የሚረዳ ነው፡፡
አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን
.

Copyright © All rights reserved.

Created with