🎯ሰልጣኞች ለምን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጆችን መምረጥ አለባቸው?
✅ሰልጣኞች የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጆችን መምረጥ አለባቸው! ምክንያቱም ተግባራዊ የሆኑና ከኢንዱስትሪ ጋር ቀጥታ ተዛማጅነት ያላቸውን ሙያዎች የሚያገኙባቸው፣ በቀጥታ ወደ ሥራ የሚገቡባቸው፣ ሥራ ፈጣሪነት እና ወደ ሥራ ገበያ በፍጥነት እንዲገቡ የሚያስችሏቸው በመሆኑ!
🔧 የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሙያዊ ብቃትን የሚያዳብር ስልጠና የሚሰጥ በመሆኑ!
🔧 የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ከበርካታ የአካዳሚክ መስመሮች ይልቅ አጠር ያሉና ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን መንገዶች በማቅረብ ሰዎችን የሥራ ባለቤት የሚያደርግ በመሆኑ!
🔧 የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ጠንካራ የስራ ትስስር እና የሥራ ስምሪት የሚያሻሽሉ የልምምድ እድሎችን የሚፈጥር በመሆኑ!
🔧 የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሰልጣኞች ለአነስተኛ ቢዝነስ ጅምሮች እና ለአካባቢ ኢኮኖሚ ልማት የሚያስፈልጉትን የስራ ፈጠራ እና ቴክኒካል ክህሎቶችን የተካኑ እንዲሆኑ ስለሚያስችል በመሆኑ የመደበኛ ትምህርት አጠናቃቂዎች ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠናን መምረጥ አለባቸው!
🌟የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና በሥራ ገበያ ላይ ያለውን የክህሎት ክፍተት በመሙላት፣ ሰፊ የሥራ ዕድሎችን የሚፈጥር እንዲሁም የዕድሜ ልክ ትምህርትና የሥራ ዕድገትን የሚያመቻች ነው፡፡ በተጨማሪም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና በግለሰብም ሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ የኢኮኖሚ ዕድገትንና ልማትን በመደገፍ ረገድ ወሳኝ ሚና የሚጫዎት ነው፡፡