የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የህዳሴውን ግድብ መጠናቀቅ “በህብረት ችለናል፡ የህዳሴ ግድብ ታሪካዊ ድል” በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ አከበረ
አዲስ አበባ መስከረም 14 ቀን 2018 ዓ.ም
በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅን በማስመልከት “በህብረት ችለናል፡ የህዳሴ ግድብ ታሪካዊ ድል” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተከብሯል:: ይህ ታሪካዊ አጋጣሚ የኢትዮጵያውያንን አንድነትና ጽናት የሚያሳይ በመሆኑ፣ የኮሌጁ ማህበረሰብ የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ በጋራ የገለጸበት ነው::
በመርሀ ግብሩ ላይ የኮሌጁ ዋናዲን ወ/ሮ ጌጤነሽ ዘርአብዛን ጨምሮ የኮሌጁ አመራሮችእና የኮሌጁ ሰራተኞች ተገኝተዋል:: ወ/ሮ ጌጤነሽ ዘርአብዛን ባደረጉት ንግግር፣ የታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ለዓመታት ሲያልመው የኖረው ህልም እውን መሆን መሆኑን ገልጸዋል። "ይህ ግድብ የትውልዶችን ጥረትና መስዋዕትነት ያሳየ፣ ለሀገራችን ብልጽግናና ብርሃን ትልቅ ተስፋ የሰነቀ ታላቅ ፕሮጀክት ነው" ሲሉ ዋና ዲኗ አጽንኦት ሰጥተዋል። የኮሌጁ አመራሮችና ሰራተኞችም የተሰማቸውን ታላቅ ደስታና ኩራት በመግለጽ፣ ግድቡ የኢትዮጵያን አቅምና በራስ የመተማመን መንፈስ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።
በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የተካሄደው ይህ የድል በዓል፣ ኢትዮጵያውያን በጋራ ቆመው ታላቅ ነገር ማሳካት እንደሚችሉ የሚያሳይ ግልጽ ማሳያ ነው። ታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ለቀጣይ የሀገር ልማትና ብልጽግና ትልቅ ማበረታቻና ትምህርት እንደሚሆን የክብረ በዓሉ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
<< ከፍታን ማፅናት ነገን ማላቅ >>
አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን!