🛠ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዜጎች የሙያ ባለቤት የሚሆኑበትና እና የኢኮኖሚ ልማት የመሰረት ድንጋይ ነው። በዚህም ስራ ፈጠራን ያሳድጋል፣ በትምህርትና ስልጠና አጠናቃቂዎች እና በስራ መካከል ያለውን ልዩነት ያስተካክላል!
🌍 የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የስራ ፈጣሪዎችና የቀጣሪ ፍላጎት ለማሟላት ከገበያ ፍላጎት ጋር የተጣጣመ ተግባራዊ ሥልጠና በመስጠት ለቀጣይ የከተማ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ያሉ ናቸው፡፡
🎓 የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ለወጣቶች (ዜጎች) ለምን ያስፈልጋል?
🛠የወጣቶች ሥራ ስምሪት፡- ብዙ ወጣት ባለበት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቀጥታ ለሥራ ዝግጁ የሆኑና ክህሎትን ያዳበሩ ወጣቶች እንዲፈጠሩ የሚያስችል በመሆኑና ከኮሌጅ በተመረቁ ሰልጣኞችና በኢንዳስትሪው መካከል ያለውን ክፍተት የሚሞሉ መሆናቸው ስራ አጥነት እንዲቀንስ ያደርጋሉ፤
🛠የምጣኔ ሀብት ዕድገት፡- የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ምርታማነትን እና ፈጠራን የተላበሱ የሰለጠኑ ባለሙያዎችን በማቅረብ ለኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ግቦች ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋሉ፤
🛠 ሥራ ፈጣሪነት፡- ብዙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተመራቂዎች የራሳቸውን ሥራ እንዲጀምሩ በማድረግ በራስ የመተማመንን ባህል እንዲያዳብሩ ያደርጋሉ፤
🛠 ማህበራዊ አካታችነት፡- የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና መርሃ ግብሮች ሴቶችን እና አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ለተገለሉ ወገኖች ተደራሽ ናቸው፣ ፍትሃዊነትን እና ማህበራዊ እንቅስቃሴንም የሚያበረታቱ ናቸው፤
🚀ስለዚህ ዛሬ በመሰልጠን የሙያና የስራ ባለቤት ባለቤት መሆን ከፈለክ/ሽ ምርጫው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ነው!
<<ከፍታን ማፅናት፤ ነገን ማላቅ>>
.