የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ አመራርና ባለሙያዎች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ክትትልና ድጋፍ አደርገዋል፤
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29/02/18ዓ/ም፤ የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ አመራሮችና ባለሙያዎች የኮሌጁን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ክትትልና ድጋፍ አድርገዋል። የክትትልና ድጋፍ ስራው በኮሌጁ በቴክኒካል ክህሎት፣ ካይዘን፣ ኢንተርፕርነየርሽፕ እና ቴክኖሎጅ የድጋፍ ማዕቀፎች አገልግሎት እያገኙ ያሉ ኢንተርፕራይዞች (MSEs) ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በዚህም የኢንዳስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት የሚሰጡ አሰልጣኞችና የድጋፉ ተጠቃሚ ኢንትፕራይዞች በትብብር የመስራት ደረጃዎችና ያመጡት ውጤት የተመላከተ ሲሆን የክትትልና ድጋፍ ቡድኑም በአገልግሎቱ የሚነሱ ችግሮች እንዲቀረፉና አዎንታዊ አስተዋጽኦዎች የሚጎለብቱበትን አግባብ አመላክቷል፡፡
አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በበጀት ዓመቱ የሚሰጠውን የኢንዳስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት በማጠናከር ኢንተርፕራይዞች ተኪምርት እንዲያመርቱ፣ ሀብት እንዲያፈሩና ለሌሎች አንቀሳቃሽና ኢንተርፕራይዞች አውትሶርስ የሚያደርጉ እንዲሆኑ ይሰራል፡፡
<< ከፍታን ማፅናት ነገን ማላቅ >>
አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን



.