Call us:
+929132651
|
Mail us for help:
aradamanufacturing@aatvetb.edu.et
|
Help center
360° Support - We are here to assist you.
Arada Manufacturing College
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
Announcement
Back
Announcement
News
Notice
Event
Online Admission
Back
Online Admission
Application Form
Registration Form
Resource
Back
Resource
Publication
Policy&Strategy
Educational Statics
Legal Document
Gallery
Support
Back
Support
Submit Ticket
My Tickets
More
Service
About
Contact Us
Status
አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ
Login
Announcement
New Trainees
New Trainees
22nd October, 2025
የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የቅበላ ቅስቀሳ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፤
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2018
የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ከአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት እና ከአካባቢው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር አዲስ ተመራቂዎችን ወደ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መርሃ ግብር ለመሸጋገር የሚያስችል የጋራ የቅስቀሳ ስራዎች በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፤
ይህ የተቀናጀ ጥረት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠናን እንዲቀላቀሉ በማድረግ የምዝገባ ሂደትን ለማቀላጠፍ እና ከኢትዮጵያ የስራ ገበያ ፍላጎት ጋር የሚጣጣም የተግባር ክህሎት ስልጠና እንዲወስዱ ለማድረግ ያለመ ነው።
በዚህ ቅስቀሳ ስራ ተማሪዎች በአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በሚሰጡ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና መርሃ ግብሮች ኦረንቴሽን፣ የሙያ መመሪያ እና ቀጥተኛ የምዝገባ ድጋፍ ያገኛሉ፡፡
የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ም/ዲን የሆኑት አቶ አለሙ ሀይሉ እንዳብራሩት "ይህ ትብብር ሰልጣኞች ስለወደፊት ህይወታቸው በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲያደርጉ እና ፍላጎታቸውን እና የገበያ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ ከትክክለኛው የሙያ መስመር ጋር እንዲጣጣሙ ያደርጋል" ብለዋል።
ይህ የቅስቀሳ ስራ የሙያ ስልጠና ተደራሽነትን ለማስፋት እና የወጣቶችን ስራ አጥነት በመቀነስ ረገድ መልካም የሚባል ተግባር መሆኑ ተመላክቷል፡፡
<<ከፍታን ማፅናት፤ ነገን ማላቅ>>
.