Announcement የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2018 የመጀመሪያ ሩብ አመት የስራ አፈጻጸምን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ፤

የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2018 የመጀመሪያ ሩብ አመት የስራ አፈጻጸምን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ፤

23rd October, 2025

የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ 2018 የመጀመሪያ ሩብ አመት የስራ አፈጻጸምን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ፤


አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13/2018.

አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ 2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት የስራ አፈጻጸምን በቅንጅት ከሚፈጸሙ ተግባራቶች አኳያና አጠቃላይ የኮሌጁን የስራ አፈጻጸም መሰረት በማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማውን አካሂዷል። በዚህ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ከአራዳ ክፍለ ከተማ ሥራና ክህሎት /ቤት፣ ኢንዳስትሪ /ቤት፣ ወጣቶችና ስፖርት /ቤት፣ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎፍቃድ ማስተባበሪያ /ቤት፣ የት/ትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን የካ ቅርንጫፍ /ቤት፣ የአዲስ አበባ /አስተዳደር አካል ጉዳተኞች ማህበር የተውጣጡ የስራ ሃላፊዎችና ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን፤
ተሳታፊዎች ኮሌጁ ባለፉት ሶስት ወራት በቅንጅታዊ አሰራር የፈጸማቸውን ስራዎችና ሌሎች መደበኛ ስራዎችን አስመልክቶ አሉ ያሏቸውን አዎንታዊና አሉታዊ አፈጻጸሞች በመገምገም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል በቀጣይም የቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ለተሸለ አገልግሎት መትጋት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡


አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በበጀት ዓመቱ የያዛቸውን ዕቅዶች ለማሳካት ያለውን ቁርጠኝነት በማረጋገጥና ይህን ትብብር በማጠናከር እንዲሁም ጠንካራ የአፈፃፀም ክትትል ስርዓቶችን ተግባራዊ በማድረግ ዓመቱን በውጤታማነት ለማጠናቀቅ ማቀዱ ተብራርቷል፡፡


በያዝነው የበጀት ዓመቱ ወርም አዲስ ሰልጣኞችን ወደ ኮሌጁ እንዲመጡና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በጋራ መፈጸም ያለባቸው ጉዳዮች ተነስተው ውይይትና የውሳኔ ሀሳብ ተሰጥቶባቸዋል፡፡


አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ!


<<ከፋታን ማጽናት፣ነገን ማላቅ>>

.

Copyright © All rights reserved.

Created with